ዘሌዋውያን 15:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፈሳሽዋም ብትነጻ ሰባት ቀን ትቈጥራለች፥ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ትሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከደሟ ፍሳሽ ሳትነጻ ሰባት ቀን ትቍጠር፤ ከዚያም በኋላ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ትሆናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደምዋም መፍሰስ ቢቆም እስከ ሰባት ቀን ትቈይ፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈሳሽዋም ብትነጻ ሰባት ቀን ትቈጥራለች፤ ከዚያም በኋላ ንጽሕት ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈሳሽዋም ብትነጻ ሰባት ቀን ትቈጥራለች ከዚያም በኋላ ንጹሕ ትሆናለች። |
ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።