የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
ሰቈቃወ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮድ። አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፥ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮድ በሀብቷ ሁሉ ላይ፣ ጠላት እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ የከለከልሃቸው፣ ጣዖት የሚያመልኩ አሕዛብ፣ ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የሕዝቡን ሀብት ዘረፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ አሕዛብ እንኳ ቤተ መቅደስዋን ሲወሩ ታዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮድ። አስጨናቂው በምኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮድ። አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፥ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና። |
የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ ከፍ ባለ ድምፅ አነበቡ፤ አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘለዓለም እንዳይገባ የሚል በዚያ ተጽፎ ተገኘ።
የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያመጡአቸዋል።
የአምላካችንን የጌታን በቀል ስለ መቅደሱም ሲል የሚበቀለውን በቀል በጽዮን ለመናገር ከባቢሎን ምድር የሚመጡትን የኰብላዮችና የስደተኞች ድምፅ አድምጡ።
ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ።
ምግቤን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ ቤቴን እንዲያረክሱ በመቅደሴ ውስጥ እንዲሆኑ ያልተገረዘ ልብ፥ ያልተገረዘ ሥጋ ያላቸውን ባዕዳንን አግብታችኋል፥ በርኩሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል።
ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዝተውት ነበር።