ዮዲት አገልጋይዋን ሌላ ጊዜ እንደምታደርገው እስክትወጣ ድረስ ከመኝታ ቤቱ ውጭ ቆማ እንድትጠብቃት ነገረቻት፤ ለጸሎቷ እንደምትወጣ ነግራታለችና፤ ለባጎስም ይህንኑ ነገረችው።
ዮዲትም አገልጋይዋን ወደ ውጭ ወጥታ በማደሪያዋ ትቆም ዘንድ አዘዘቻት፤ “ወደምጸልይበት እወጣለሁ” ብላታለችና እንደ ወትሮው በምትመጣበት ጊዜ ትጠብቃት ዘንድ አዘዘቻት፤ ለባግዋም እንደዚሁ ነገረችው።