በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር።
ኢያሱ 9:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፤ ከተሞቻቸው ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያት-ይዓሪም ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እስራኤላውያን ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮትና ኢያሪም ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፥ የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም ነበረ። |
በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር።
ደግሞም በጌታ ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የቂርያት-ይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃላት ሁሉ ትንቢት ተናገረ።
ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ ነበረች፥ ከጋይም ስለ ምትበልጥ፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኃያላን ስለ ነበሩ፥ እጅግ ፈራ።
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤
ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፤ መጨረሻውም ቂርያት-ይዓሪም በምትባል በቂርያትበኣል በይሁዳ ልጆች ከተማ ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።
ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚህ የተነሣ ነው።
ከዚያም ወደ ቂርያትይዓሪም ሰዎች መልእክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የጌታን ታቦት መልሰውልናል፤ መጥታችሁ ወደ እናንተ ውሰዱት” አሏቸው።
የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የጌታን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የጌታን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።