ኢያሱ 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ላይ ተሻገረ፤’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስ በደረቅ ምድር ተሻገረ’ ብላችሁ ንገሯቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ የዮርዳኖስን ወንዝ በደረቅ ምድር የተሻገሩበት ጊዜ መኖሩን ትነግሩአቸዋላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ትነግሯቸዋላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ፥ |
የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹ ከፈረሰኞቹም ጋር ወደ ባሕር ገቡ፥ ጌታም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ሄዱ።
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።
እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት በሚሻገሩ ጊዜ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳንስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።