ኢያሱ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከሕዝቡ ዐሥራ ሁለት ሰዎች፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ምረጥ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከሕዝቡ መካከል ከየነገዱ አንዳንድ ሰው፣ በድምሩ ዐሥራ ሁለት ሰው ምረጥ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሰው በመውሰድ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ምረጥ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ውሰድ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጥና፦ |
“ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ።”
እንዲህም ብለህ እዘዛቸው፦ ‘በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።’”