ኢያሱ 18:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገባዖን፣ ራማ፣ ብኤሮት፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጨማሪም ገባዖን፥ ራማ፥ በኤሮት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥ |
በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር።
ባዕሻ ይሁዳን በመውረር ራማን ምሽግ አድርጎ መሥራት ጀመረ፤ ይህንንም ያደረገው ወደ ይሁዳ ማንም እንዳይገባና ከዚያም ማንም እንዳይወጣ ለመከልከል ነው።
ጌታም፥ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው፥ በገባዖንም ሸለቆ እንዳደረገው፥ ሥራውን ለመሥራት፥ አስደናቂ ሥራውን! ተግባሩን ለመፈጸም፥ አስገራሚ ተግባሩን! ይነሣል፤ ይነሣሣልም።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።”
ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ ነበረች፥ ከጋይም ስለ ምትበልጥ፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኃያላን ስለ ነበሩ፥ እጅግ ፈራ።
በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊዩ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የናሲብ ልጅ ሲሆን ከኤፍሬም ነገድ ነበረ።