ኢሳይያስ 28:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ጌታም፥ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው፥ በገባዖንም ሸለቆ እንዳደረገው፥ ሥራውን ለመሥራት፥ አስደናቂ ሥራውን! ተግባሩን ለመፈጸም፥ አስገራሚ ተግባሩን! ይነሣል፤ ይነሣሣልም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣ በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 እግዚአብሔር በጰራጺም ተራራ ላይና በገባዖን ሸለቆ ላይ እንዳደረገው፥ አሁንም ያልተለመደ ሥራውን ለመሥራትና ለሰው እንግዳ የሆነው ተግባሩን ለመፈጸም ይነሣል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እግዚአብሔርም በኃጥኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፤ በገባዖን ሸለቆም ይኖራል፤ ሥራውን ማለት መራራ ሥራውን በቍጣ ይሠራል፤ ቍጣውም ድንቅን ያደርጋል፤ መርዙም ልዩ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እግዚአብሔርም ሥራውን ማለት እንግዳ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፥ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ በፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፥ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል። ምዕራፉን ተመልከት |