ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ይነፍስ፥ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፤ ንጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤
ኢያሱ 17:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍም ልጆች እንዲህ አሉት፦ “ተራራማው አገር አይበቃንም፤ በሸለቆውም ውስጥ የሚኖሩት፥ በቤትሳና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ የሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰረገሎች አላቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍም ዘሮች፣ “ኰረብታማው አገር አይበቃንም፤ ደግሞም በሜዳው ላይ ያሉት በቤትሳንና በሰፈሮቿ፣ እንዲሁም በኢይዝራኤል ሸለቆ የሚኖሩት ከነዓናውያን ሁሉ የብረት ሠረገሎች አሏቸው” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ኮረብታማይቱ አገር ለእኛ በቂ አይደለችም፤ ከዚህም ሁሉ ጋር በኢይዝራኤል ሸለቆ በቤትሻንና በዙሪያዋ ባሉት ታናናሽ ከተሞችና በሜዳማው አገር የሚኖሩ ከነዓናውያን ብዙ የብረት ሠረገሎች አሉአቸው” ሲሉ መለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ተራራማው የኤፍሬም ሀገር አይበቃንም፤ በሸለቆው ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤትሳንና በመንደሮችዋ፥ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የተመረጡ ፈረሶችና ሰይፍ አሏቸው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍም ልጆች፦ ተራራማው አገር አይበቃንም፥ በሸለቆውም ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤትሳና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰረገሎች አላቸው አሉት። |
ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ይነፍስ፥ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፤ ንጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤
የጌታም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።
የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፥ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ንጉሦች ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፥ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም።
የሶርያም ንጉሥ ባርያዎች እንዲህ አሉት፦ “አምላካቸው የተራሮች አምላክ ነው፥ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፥ ነገር ግን በሜዳ ላይ ከእነርሱ ጋር ብንዋጋ በእርግጥ እንበረታባቸዋለን።
በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፦ የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፥ እንዲሁም በቤት ሻን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ፥ በጻርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተ ደቡብ ያለው ግዛት፥ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅመዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ።
ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የእርሷም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤’” ይህን ሁሉ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወጣቱ ነቢይ በሩን በመክፈት ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ።
ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርሷነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”
ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ቀኖች ይመጣሉ፥ ይላል ጌታ፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል ጌታ።
በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።
ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ብዙ ሕዝብስ ከሆንህ ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦህ እንደሆነ ወደ ዱር ወጥተህ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለአንተ ስፍራ መንጥር።”
ኢያሱም የዮሴፍ ወገን ለሚሆኑ ለኤፍሬምና ለምናሴ እንዲህ አላቸው፦ “አንተ ብዙ ሕዝብ ነህ፥ ጽኑም ኃይል አለህ፤ አንድ ዕጣ ብቻ አይወጣልህም።
ነገር ግን ተራራማው አገር ለአንተ ይሆናል፥ ዱር እንኳን ቢሆንም ትመነጥረዋለህ፥ ለአንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ቢኖሩአቸው የበረቱም ቢሆኑ ታሳድዳቸዋለህ።”
ጌታ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፤ ስለዚህ ኰረብታማውን አገር ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳማው ምድር የሚኖሩት ሰዎች ከብረት የተሠሩ ሠረገሎች ስለ ነበሯቸው ከዚያ አሳደው ሊያስወጧቸው አልቻሉም።
በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ያላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ።