መሳፍንት 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ጌታ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፤ ስለዚህ ኰረብታማውን አገር ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳማው ምድር የሚኖሩት ሰዎች ከብረት የተሠሩ ሠረገሎች ስለ ነበሯቸው ከዚያ አሳደው ሊያስወጧቸው አልቻሉም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እግዚአብሔር ከይሁዳ ሰዎች ጋራ ነበር፤ ስለዚህ ኰረብታማውን አገር ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳው ምድር የሚኖሩት ሰዎች ከብረት የተሠሩ ሠረገሎች ስለ ነበሯቸው ከዚያ አሳድደው ሊያስወጧቸው አልቻሉም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እግዚአብሔር ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ስለ ነበረ የተራራማውን አገር አሸንፈው ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳማው ሜዳ አገር የነበሩት ኗሪዎች የብረት ሠረገሎች ስለ ነበሩአቸው ሊያስወጡአቸው አልቻሉም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁዳም ተራራማውን ሀገር ወረሰ፤ በሸለቆው የሚኖሩትን ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊወርሳቸው አልቻለም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፥ ይሁዳም ተራራማውን አገር ወረሰ፥ በሸለቆው የሚኖሩት ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊያወጣቸው አልቻለም። ምዕራፉን ተመልከት |