ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።
ኢያሱ 15:57 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃይን፥ ጊብዓና ቲምና ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥር ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ያጠቃልላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጋባ፥ ተምና፥ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥ ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፥ አሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።
ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።