Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 38:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፣ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከኤራ ጋራ የበጎቹን ጠጕር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዘመ​ን​ዋም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ የይ​ሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁ​ዳም ተጽ​ናና፤ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ወደ​ሚ​ሸ​ል​ቱት ሰዎ​ችም ወደ ተምና ወጣ፤ እር​ሱም ዓዶ​ሎ​ማ​ዊው በግ ጠባ​ቂው ኤራ​ስም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከብዙ ዘመንም በኍላ የይሁዳ ሚስት የሴዋ ልጅ ሞተች ይሁዳም ተጽናና የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱት ሰዎችም ወደ ተምና ወጣ እርሱም ዓዶሎማዊው ወዳጁም ኤራስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 38:12
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።


ንጉሥ ዳዊትም በልጁ ሞት ከደረሰበት ኀዘን ተጽናና፤ ከዚያም መንፈሱ ወደ አቤሴሎም ለመሄድ ናፈቀ።


ሶምሶን ወደ ቲምና ወረደ፤ እዚያም አንዲት ወጣት ፍልስጥኤማዊት አየ።


ይስሐቅም ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን አገባት፥ ርብቃንም ወሰዳት፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደዳትም፥ ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና።


አቢጌልም ወደ ናባል በተመለሰች ጊዜ፥ እነሆ፤ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ትልቅ ግብዣ አድርጎ አገኘችው፤ ክፉኛም ሰክሮ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ነበር። ስለዚህ እስኪ ነጋ ድረስ ምንም አልነገረችውም።


ኤሎንን፥ ትምናን፥ አቃሮንን፥


ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥


የርሙት፥ ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥


በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ፥ ኤራስ ወደ ተባለ ዓዶሎማዊ ሰው ወረደ፤ እርሱም ዘንድ ለመኖር ቤቱ ገባ።


ላባም በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፥ ራሔልም የአባትዋን ቤት ጣዖቶች ሰረቀች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች