ኢያሱ 15:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዐይን፥ ሪሞን፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ በአጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልባዎት፥ ሺልሒም፥ ዓይንና፥ ሪሞን ተብለው የሚጠሩት በድምሩ ኻያ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙት ታናናሽ ከተሞችንም ሁሉ ያጠቃልላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላቦስ ሳሌ፥ ኤርሞትም ሃያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞን፥ ሀያዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ፥ እንደ ዓረባ ትሆናለች፤ እርሷም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው የበሯ ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።