ኢያሱ 14:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አከፋፈሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስታቸውም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዕጣ ተከፋፈለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ ያለው ግዛት በሙሉ ለዘጠኙ ነገድ ተኩል በዕጣ ተከፈለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አከፋፈሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አካፈሉአቸው። |
ርስት አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድሪቱ የተቀደሰውን ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ ጌታ ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ዙሪያ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል።
ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።