Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 1:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ዕጣም ተጣጣሉላቸው፤ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቆጠረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከዚያም ዕጣ ጣሉላቸው፤ ዕጣውም ለማትያስ ወጣ፤ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋራ ተቈጠረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ዕጣም በጣሉ ጊዜ ዕጣው ለማትያስ ወጣ፤ ስለዚህ እርሱ ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ዕጣም አጣ​ጣ​ሏ​ቸው፤ ዕጣ​ዉም በማ​ት​ያስ ላይ ወጣ፤ ከዐ​ሥራ አንዱ ሐዋ​ር​ያት ጋራም ተቈ​ጠረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 1:26
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱ ዕጣ ለጌታ ሌላው ዕጣ ለዐዛዜል ይሆናል።


ኢያሱም በጌታ ፊት በሴሎ ዕጣ ጣለላቸው፤ በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደየድርሻቸው ምድሩን ከፈለ።


እርስ በእርሳቸውም፦ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደመጣብን እንድናውቅ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።


ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና በእግዚአብሔር የተሾሙ አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።


ነገር ግን ጴጥሮስ ከዐሥራ አንዱ ጋር ቆመ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው “የይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ቃሎቼንም አድምጡ።


ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፥ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው።


በከነዓንም አገር ሰባት አሕዛብን አጥፍቶ ምድራቸውን አወረሳቸው።


ጌታ በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አከፋፈሉአቸው።


እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥


የሕዝቡ መሪዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀረው ሕዝብ ከአሥሩ አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲቀመጡ ዕጣ ተጣጣሉ።


ዕጣ በጉያ ይጣላል፥ መደብዋ ሁሉ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


ሐዋርያትም በኢየሱስ ዙሪያ ተሰብስበው የሠሩትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት።


ኢዮስጦስም የሚሉትን በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቆሙ።


ለከተማይቱም ቅጥር ዐሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፤ በእነርሱም ውስጥ የዐሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች