የይሁዳን ምድር ትቶ ወደ ገሊላ እንደገና ሄደ።
ጌታም ይህን እንዳወቀ ይሁዳን ለቅቆ ወደ ገሊላ ተመልሶ ሄደ።
ስለ እርሱ የተባለውን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ባወቀ ጊዜ ኢየሱስ የይሁዳን ምድር ትቶ ወደ ገሊላ ተመልሶ ሄደ።
የይሁዳንም ምድር ትቶ ዳግመኛ ወደ ገሊላ ሄደ።
ከዚያች ከተማ ቢያሳድዱአችሁ ወደ ሌላዪቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተሞች አትጨርሱም።
ኢየሱስም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕር ፈቀቅ አለ፤ ከገሊላና ከይሁዳ የመጡም ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤
ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ በገሊላና በሰማርያ መካከል አለፈ።
በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አገኘውና “ተከተለኝ” አለው።
ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደነበረው ስፍራ፥ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ፥ እንደገና ሄደ፤ በዚያም ተቀመጠ።
ከዚያ ወዲያም ኢየሱስ በአይሁድ መካከል ተገልጦ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ በምድረ በዳ አጠገብ ወዳለች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።
ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፤ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።
ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፤ ምስክርነቱንም የሚቀበለው የለም።
እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደመጣ ሰምቶ፥ ልጁ ሊሞት ስለ ቀረበ፥ ወደ እርሱ ሄደ፤ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው።
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በገሊላ ይመላለስ ነበር። አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበር።