አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።
ኢዩኤል 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተቅበዘበዙ፥ የበግም መንጎች እየተሰቃዩ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንጎች እንደ ምን ጮኹ፣ ከብቶቹ ተደናግጠዋል፤ መሰማሪያ የላቸውምና፤ የበግ መንጎች እንኳ ተቸግረዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግጦሽ ሣር በማጣት ከብቶች ያላዝናሉ፤ የበጎች መንጋ ሳይቀሩ ተርበው በብርቱ ሥቃይ ላይ ይገኛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ለራሳችን ምን እንሰብስብ? የእንስሳት ጠባቂዎች አለቀሱ፤ ማሰማሪያ የላቸውምና፥ የበጎች መንጋዎችም ጠፍተዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተጠራጠሩ፥ የበግም መንጎች ጠፍተዋል። |
አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።
ንጉሥ ሰሎሞንና በፊቱ የተሰበሰበው መላው የእስራኤል ሕዝብ፥ ከእርሱ ጋር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ሆነው፥ ከብዛቱም የተነሣ የማይቆጠር ብዙ በግና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ነበር።
ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ እጽዋት ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ “ፍጻሜያችንን አያይም” ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ተጠራርገው ጠፍተዋል።
እንዲህም አለ፦ “ጌታ በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ድምፁን ያስተጋባል፤ የእረኞችም ማሰማርያዎች ይጠወልጋሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”
የበለስ ዛፍ ባታብብም፥ በወይን ተክሎች ላይ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ምርት ቢቋረጥ፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ከብቶችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥