ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለ ሥልጣን፥ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፥ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረውን መኰንንና ሌሎችንም ሥልሳ ሰዎችን ወሰደ፤
ኤርምያስ 52:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማይቱም በወታደሮች ላይ ተሾሞ ከነበረው አንዱን አዛዥ፥ በከተማይቱም ውስጥ ከተገኙት የንጉሡ አማካሪዎች ሰባቱን ሰዎች፥ የአገሩንም ሕዝብ ለጦርነት የሚመለምለውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስልሳ ሰዎች ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማው ውስጥ ከቀሩትም ሕዝብ፣ የተዋጊዎቹ ኀላፊ የነበረውን መኰንን፣ ሰባቱን የንጉሡን አማካሪዎች ከአገሬው ሕዝብ ወታደር የሚመለምለውን መኰንን ጸሓፊና በከተማው ውስጥ የተገኙትን ሌሎች ስድሳ ሰዎች ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነ አንድ ባለ ሥልጣንና እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ ውስጥ የተገኙትን ሰባቱን የንጉሡን አማካሪዎች፥ የወታደራዊ ጉዳዮች ጸሐፊ የነበረውን የጦር አዛዡን ረዳትና ሌሎችንም ሥልሳ ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከከተማዪቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማዪቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፥ የሀገሩን ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማዪቱም ከተገኙት የሀገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎችን ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማይቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማይቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፥ የአገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎች ወሰደ። |
ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለ ሥልጣን፥ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፥ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረውን መኰንንና ሌሎችንም ሥልሳ ሰዎችን ወሰደ፤
ባሮክም የኤርምያስን ቃላት በላይኛው አደባባይ በጌታ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ፥ በገማርያ ጓዳ በጌታ ቤት ውስጥ በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ ከመጽሐፉ አነበበ።