Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 52:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን በማዕረጉም ሁለተኛ የነበረውን ካህን ሶፎንያስን የደጃፉም ጠባቂዎች የነበሩትን ሦስቱን ሰዎች ወሰደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የክብር ዘበኞቹ አዛዥም ሊቀ ካህኑን ሠራያን፣ በማዕርግ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የበር ጠባቂዎች አስሮ ወሰዳቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚያም ሁሉ ጋር የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሠራያን፥ በማዕርግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሌሎችንም ሦስት የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎችን አስሮ ወሰደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ታላ​ቅን ካህን ሠራ​ያን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን፥ ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ወሰደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 52:24
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ሊቀ ካህናቱን ሒልቅያን፥ ረዳቶቹ የሆኑትን ካህናትና የቤተ መቅደሱን መግቢያ በር ዘብ የሚጠብቁ ተረኞችን ጠርቶ ለበዓልና አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ፥ እንዲሁም ለከዋክብት ማምለኪያ ያገለግሉ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ንጉሡም እነዚያን ዕቃዎች ሁሉ ከኢየሩሳሌም ውጪ ባለው በቄድሮን ሸለቆ በእሳት አቃጥሎ ዐመዱን ወደ ቤትኤል ወሰደው፤


የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሤራያን በማዕረግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው፤


ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤


ከነዚህም ነገሮች በኋላ በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ መንግሥት ዕዝራ የሠራያ ልጅ፥ የዓዛርያ ልጅ፥ የሒልቂያ ልጅ፥


አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።


ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዐይኖችህም ያያሉ፤ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።


ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል በላከበት ጊዜ ነው፦


“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፦


ካህኑም ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ በነቢዩ በኤርምያስ ጆሮ አነበበው።


የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን፥ ለጠላቶቻቸው እጅ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።


ወደ ጌታም ቤት የደጁ ጠባቂ በሆነው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው በአለቆች ጓዳ አጠገብ ወደሚገኘው፥ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ አስገባኋቸው።


ንጉሡም ሴዴቅያስ፦ “እባክህ፥ ወደ አምላካችን ወደ ጌታ ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።


በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዓሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚያገለግለው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።


የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን የሕዝቡን ድኆች፥ በከተማይቱም ውስጥ የተረፈውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የተረፉትንም የእጅ ሞያተኞች አፈለሰ።


ዔ። የእግዚአብሔር ፊት በተናቸው እርሱም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፥ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፥ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ያኖራችኋቸው የተገደሉት እነርሱ ሥጋው ናቸው፥ ድስቱ ይህች ከተማ ናት፥ እናንተን ግን ከመካከልዋ አወጣችኋለሁ።


የተመረጠውን መንጋ ውሰድ፥ አጥንቶቹም እንዲበስሉ ከስሩ ማገዶ ጨምር፤ በደንብ ይንተክተክ፥ አጥንቶቹም በውስጡ ይብሰሉ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በእረኞች ላይ ነኝ፥ መንጋዎቼን ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ መንጋዎቼን ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያስማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች