ከዚህ በኋላ፥ ይላል ጌታ፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህችም ከተማ የቀሩትን፥ አገልጋዮቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።’
ኤርምያስ 52:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው ወደ ባቢሎንም ወሰደው፥ እስኪሞትም ድረስ በእስር ቤት አኖረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ በናስ ሰንሰለትም አሰረው። የባቢሎንም ንጉሥ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ በዚያም እስከ ዕለተ ሞቱ በእስር ቤት አቈየው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ በእግር ብረት በማሰር ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እስከ ሞተበትም ጊዜ ድረስ በባቢሎን እስረኛ አደረገው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው፤ ወደ ባቢሎንም ወሰደው፤ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴዴቅያስንም ዓይኖች አወጣ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው ወደ ባቢሎንም ወሰደው፥ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው። |
ከዚህ በኋላ፥ ይላል ጌታ፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህችም ከተማ የቀሩትን፥ አገልጋዮቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።’
ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቁጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ።
እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ መሐላውን የናቀበት፥ ከእርሱ ጋር የነበረውን ቃል ኪዳኑን ያፈረሰበት፥ ያነገሠው ንጉሥ በሚኖርበት ስፍራ በባቢሎን መካከል በእርግጥ ይሞታል።
መሣሪያ፥ ሠረገላና መንኰራኵር ይዘው፥ ብዙ ሕዝብ ሆነው በአንቺ ላይ ይመጣሉ፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቁርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል።