Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 52:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይ​ኖች አወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ወሰ​ደው፤ እስ​ኪ​ሞ​ትም ድረስ በግ​ዞት ቤት አኖ​ረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ በናስ ሰንሰለትም አሰረው። የባቢሎንም ንጉሥ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ በዚያም እስከ ዕለተ ሞቱ በእስር ቤት አቈየው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው ወደ ባቢሎንም ወሰደው፥ እስኪሞትም ድረስ በእስር ቤት አኖረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚያም በኋላ የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ በእግር ብረት በማሰር ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እስከ ሞተበትም ጊዜ ድረስ በባቢሎን እስረኛ አደረገው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የሴዴቅያስንም ዓይኖች አወጣ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው ወደ ባቢሎንም ወሰደው፥ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 52:11
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይን አወጣ፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስሮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው።


ዋው። ማደ​ሪ​ያ​ውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓ​ሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ያደ​ረ​ገ​ውን በዓ​ሉ​ንና ሰን​በ​ቱን አስ​ረሳ፤ በቍ​ጣ​ውም መዓት ነገ​ሥ​ታ​ቱን፥ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱን አጠፋ።


መረ​ቤ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በወ​ጥ​መ​ዴም ይያ​ዛል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ወደ ባቢ​ሎን አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ሆኖም አያ​ያ​ትም፤ በዚ​ያም ይሞ​ታል።


“እኔ ሕያው ነኝ! ያነ​ገ​ሠ​ውና መሐ​ላ​ውን የና​ቀ​በት፥ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​በት ንጉሥ በሚ​ኖ​ር​በት ስፍራ ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን መካ​ከል በር​ግጥ ይሞ​ታል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ሰዎች ሁሉ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ርና በሠ​ረ​ገላ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ጋሻና አላ​ባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙ​ሪ​ያሽ ጥበቃ ያደ​ር​ጋሉ፤ ፍር​ድ​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ፍር​ዳ​ቸ​ውም ይፈ​ር​ዱ​ብ​ሻል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች