ኤርምያስ 41:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከላቸውም እስማኤልን፦ “በእርሻ ውስጥ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን” የሚሉት ዐሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተገደሉት ጋራ የነበሩ ዐሥር ሰዎች ግን እስማኤልን፣ “እባክህ አትግደለን! በዕርሻችን ውስጥ የሸሸግነው ስንዴና ገብስ፣ የወይራ ዘይትና ማር ስላለን እባክህን አትግደለን” አሉት። እርሱም ተዋቸው፤ ከሌሎቹም ጋራ አልገደላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነዚያ ሰማኒያ ሰዎች መካከል በተለይ ዐሥሩ ሰዎች “እባክህ አትግደለን! እኛ በእርሻ ውስጥ የደበቅነው ብዙ ስንዴ፥ ገብስ፥ የወይራ ዘይትና ማር. አለን” ብለው እስማኤልን ለመኑት። እርሱም ምሕረት አደረገላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም የተገኙ ዐሥር ሰዎች ቀርበው እስማኤልን እንዲህ አሉት፥ “በሜዳው ድልብ አለንና፥ ገብስና ስንዴ፥ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን፤” እርሱም በወንድሞቻቸው መካከል እነርሱን መግደል ተወ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላቸውም እስማኤልን፦ በሜዳ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን የሚሉት አሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም። |
በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ለመመከት የሠራው ምሽግ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።
ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ነፍስ ከምግብ ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?