Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 13:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፥ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሀብታም በገንዘብ ሕይወቱን ለማዳን ይጣጣራል፤ ድኻ ግን የሚወሰድበት ሀብት ስለሌለው አይጨነቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 13:8
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።


ነገር ግን ምንም ሀብት የሌላቸውን የመጨረሻ ድኾች፥ አትክልት ኰትኳቾችና መሬት አራሾች ይሆኑ ዘንድ በይሁዳ ምድር ትቶአቸው ሄደ።


ሰይጣንም መልሶ ጌታን እንዲህ አለው፦ “በቆዳ ላይ ቆዳ፥ ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል።


ካሳ እንዲከፍል ቢወሰንበት ግን፥ የነፍሱን ካሳ የወሰኑበትን ያህል ይስጥ።


ራሱን ሀብታም የሚያስመስል ሰው አለ፥ ነገር ግን አንዳች የለውም፥ ራሱን ድሀ የሚያስመስል አለ፥ ነገር ግን እጅግ ባለጠግነት አለው።


ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።


የጠቢባን ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፥ የሰነፎች ስንፍና ግን ስንፍና ነው።


እርሱም ምንም ካሣ አይቀበልም፥ ስጦታም ብታበዛለት አይታረቅም።


የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ምንም የሌላቸውን አንዳንድ ድሆች በይሁዳ አገር ተዋቸው፥ በዚያው ጊዜም የወይኑን ቦታዎችና እርሻዎችን ሰጣቸው።


በመካከላቸውም እስማኤልን፦ “በእርሻ ውስጥ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን” የሚሉት ዐሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።


በመካከልሽ ትሑትና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብን አስቀራለሁ፤ በጌታም ስም ይታመናሉ።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች