በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።
ኤርምያስ 39:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሴዴቅያስም በዓሥራ አንደኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማይቱ ቅጥር ተጣሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ አንደኛው ዓመት በአራተኛው ወር፣ በወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማዪቱ ቅጥር ተሰበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስ በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ በዘጠነኛው ቀን የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሴዴቅያስም በዐሥራ አንደኛው ዓመተ መንግሥት በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማዪቱ ተለያየች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሴዴቅያስም በአሥራ አንደኛው ዓመት በአራተኛው ወር ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማይቱ ተሰበረች። |
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።
እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ወደዚህችም ከተማ እመልሳቸዋለሁ፤ እርሷንም ይወጋሉ ይይዙአታልም በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
እንዲህም ሆነ፥ በተማረክን በዓሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተማይቱ ተመታች አለኝ።
የብረት ምጣድም ውሰድ፥ በአንተና በከተማይቱ መካከል የብረት ቅጥር አድርገው፥ ፊትህንም ወደ እርሷ አቅና፥ የተከበበችም ትሆናለች፥ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።
የመከበብም ወራት ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማይቱ መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወስደህ ዙሪያውን በሰይፍ ትመታዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፥ እኔም ከኋላቸው ሰይፍ እመዝዛለሁ።
የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም፥ የአምስተኛው፥ የሰባተኛው፥ የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ፥ የሐሤትም በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ!