ኤርምያስ 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አመንዝራነትዋንም እንደ ቀላል በመቁጠሩዋ ምድሪቱን አረከሰች፤ እርሷም ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቅሌቷም ምድሪቱን አረከሰች፤ ከድንጋይና ከግንድ ጋራ አመነዘረች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቶም አላፈረችም፤ ይልቁንም ድንጋይና ዛፍ በማምለክ ምድሪቱን አረከሰች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝሙቷም ከንቱ ሆነ፤ እርስዋም ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግልሙትናዋም በመቅለልዋም ምድሪቱ ረከሰች፥ እርስዋም ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች። |
በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፥ እነርሱም ዕጣዎችሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቁርባን አፍስሰሻል፥ የእህልንም ቁርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣም?
ምድሬንም በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
ግንዱን፦ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ድንጋዩንም፦ ‘አንቺ ወለድሺኝ’ ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ‘ተነሥተህ አድነን’ ይላሉ።
ፍሬዋንና በረከትዋንም እንድትበሉ ወደ ፍሬያማ ምድር አስገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፥ ርስቴንም የተጠላች አደረጋችሁ።
ወደ ተራቈቱ ኮረብቶች አይኖችሽን አንሺ፥ ተመልከቺም፤ ያልተጋደምሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ልክ በምድረ በዳ እንደሚቀመጥ አረባዊ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ ትጠብቂያቸዋለሽ፤ በግልሙትናሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።
እነርሱም ዕራቁትነትዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ወሰዱ፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሉ፤ በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች፥ ፍርድም ተፈጸመባት።
የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፥ እነርሱም አንድ አለቃ በራሳቸው ላይ ይሾማሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናልና ከምድሪቱ ይወጣሉ።
እንጨቱን “ንቃ” ዝም ያለውንም ድንጋይ “ተነሣ” ለሚለው ወዮለት! ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ በውስጡም ምንም እስትንፋስ የለበትም።
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።