ኤርምያስ 17:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ፥ ልቡም ከጌታ የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰው የሚታመን፣ በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣ ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ትቶ በሰው የሚታመንና፥ ‘ኀይል ይሆነኛል’ ብሎ በሥጋ ለባሽ ሰው የሚመካ የተረገመ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በሰው የሚታመን የሥጋ ክንዱንም በእርሱ የሚያስደግፍ፥ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚርቅ ሰው ርጉም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። |
ከእርሱ ጋር ያለው ሥጋዊው ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን ጌታ አምላካችን ነው።” ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃላት ተበረታታ።
እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ የሸንበቆ በትር በግብጽ ተማምነሀል፤ ሰው ተማምኖ ቢመረኰዘው እጁን ወግቶ ያቈስለዋል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርኦን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።
ያመለጡት ተማርከው በሄዱባቸው በአሕዛብ መካከል ሆነው ያስታውሱኛል፤ ምክንያቱም ከእኔ በራቀው አመንዝራ ልባቸውና፥ ጣዖቶቻቸውን በተከተሉ በአመንዝራ ዐይኖቻቸው ተሰብሬአለሁና፥ በክፉ ስራቸውና በርኩሰታቸውም ሁሉ ራሳቸውን ይጸየፋሉ።
ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው።