ኢሳይያስ 59:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 እውነትም ታጥቶአል፥ ከክፋትም የራቀ ሰው ተበዝባዥ ሆኗል። ጌታም አየ፥ ፍትህም ስለ ሌለ ተከፋ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እውነት የትም ቦታ አይገኝም፤ ከክፋት የሚርቅ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ተመለከተ፤ ፍትሕ በመታጣቱም ዐዘነ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እውነት ጠፍቶአል፤ ከክፉ ሥራ የሚመለስ የሌሎች መሳለቂያ ይሆናል፤ እግዚአብሔርም ፍትሕ አለመኖሩን አይቶ አዘነ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ከእውነት ተወግደዋል፤ እንዳያስተውሉም ልባቸውን መልሰዋል። እግዚአብሔርም አየ፤ ፍርድም ስለሌለ ደስ አላለውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እውነትም ታጥቶአል፥ ከክፋትም የራቀ ሰው ለብዝበዛ ሆኖአል። እግዚአብሔርም አየ፥ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ። ምዕራፉን ተመልከት |