ከእነርሱም በኋላ፥ ዐቅመ ደካማ፥ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።
ዘፍጥረት 41:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጥሎም መልካቸው የከፋ ዐጥንታቸው የወጣ፥ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም መልካቸው የከፋ ዐጥንታቸው የወጣ፣ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም አጥንታቸው እስከሚታይ የከሱ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወንዙ ዳር ከነበሩት ላሞች አጠገብ ቆሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በኋላ እነሆ፥ መልካቸው የከፋ፥ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ተሰማርተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በኍላ እነሆ መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዝ ወጡ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ይቆሙ ነበር። |
ከእነርሱም በኋላ፥ ዐቅመ ደካማ፥ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።