በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፥ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።
ዘፍጥረት 40:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ፥ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፥ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን ዐስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሁሉ ነገር በተቃናልህ ጊዜ እኔን አስታውሰህ እርዳኝ፤ ለፈርዖንም አሳስበህ ከእዚህ ከእስር ቤት እንድወጣ አድርገኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን ዐስበኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን አሳስበህ ከዚህ እስር ቤት አውጣኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በጎ ነገር በተደረግልህ ጊዜ እኔን አስበኝ ምሕረትንም አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርዖን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ፤ |
በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፥ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።
“ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ።
ጌታዬ የምታዝንበት ምክንያት ወይም የኅሊና ጸጸት አይኖርብህም፤ ምክንያቱም በከንቱ ያፈሰስከው ደም ወይም በገዛ እጅህ የወሰድከው በቀል የለምና። ስለዚህ ጌታ ለጌታዬ በጎ ነገር ባደረገልህ ጊዜም፥ እኔንም አገልጋይህን አስበኝ።”