Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 40:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን በጎ ነገር በተ​ደ​ረ​ገ​ልህ ጊዜ እኔን ዐስ​በኝ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አድ​ር​ግ​ልኝ፤ ስለ እኔም ለፈ​ር​ዖን አሳ​ስ​በህ ከዚህ እስር ቤት አው​ጣኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን ዐስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንግዲህ፥ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፥ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነገር ግን ሁሉ ነገር በተቃናልህ ጊዜ እኔን አስታውሰህ እርዳኝ፤ ለፈርዖንም አሳስበህ ከእዚህ ከእስር ቤት እንድወጣ አድርገኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን በጎ ነገር በተደረግልህ ጊዜ እኔን አስበኝ ምሕረትንም አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርዖን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 40:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሉ​ልኝ፤ እኔ ለእ​ና​ንተ ቸር​ነት እንደ አደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ደግሞ ለአ​ባቴ ቤት ቸር​ነት እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ፥ በእ​ው​ነት ምል​ክት ስጡኝ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው።


ከወ​ን​ድ​ምህ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ፊት በሸ​ሸሁ ጊዜ ቀር​በ​ው​ኛ​ልና ለገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ለቤ​ር​ዜሊ ልጆች ቸር​ነ​ትን አድ​ር​ግ​ላ​ቸው። በማ​ዕ​ድ​ህም ከሚ​በ​ሉት መካ​ከል ይሁኑ።


አንተ ባርያ ሳለህ ብታ​ምን አያ​ሳ​ዝ​ንህ፤ የሚ​ቻ​ልህ ከሆነ ግን ነጻ​ነ​ት​ህን አግኝ።


ዳዊ​ትም፥ “ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ አንድ ሰው አለን?” አለ።


ይህ ርኵ​ሰ​ትና የልብ በደል፥ በከ​ንቱ ንጹሕ ደም ማፍ​ሰ​ስም ለጌ​ታዬ አይ​ሁ​ኑ​በት፤ የጌ​ታ​ዬም እጁ ትዳን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለጌ​ታዬ በጎ ያድ​ር​ግ​ለት፤ በጎም ታደ​ር​ግ​ላት ዘንድ ባሪ​ያ​ህን አስብ።”


እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈር​ዖን ሹመ​ት​ህን ያስ​ባል፤ ወደ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃ​ነ​ት​ህም ይመ​ል​ስ​ሃል፤ ጠጅ አሳ​ላፊ በነ​በ​ር​ህ​በት ጊዜ ስታ​ደ​ር​ገው እንደ ነበ​ረው እንደ ቀድ​ሞው ሹመ​ት​ህም የፈ​ር​ዖ​ንን ጽዋ በእጁ ትሰ​ጣ​ለህ።


የዚ​ያን ጊዜ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎቹ አለቃ እን​ዲህ ብሎ ለፈ​ር​ዖን ተና​ገረ፥ “እኔ ኀጢ​አ​ቴን ዛሬ አስ​ባ​ለሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች