እግዚአብሔርም ለእርሱ፥ “እንዲህስ አይሆንም! ማንም ቃየንን የሚገድል፥ ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ጌታም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት።
ዘፍጥረት 4:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከሆነ ቃየልን ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት፥ ላሜሕን ግን ሰባ ጊዜ ሰባት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃየንን የሚገድል ሰባት ጊዜ ቅጣት ካገኘው፣ የላሜሕ ገዳይማ ሰባ ሰባት ጊዜ ቅጣት ያገኘዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃየልን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል ከተባለ፥ እኔን የሚገድል ደግሞ ሰባ ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃየልን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፤ ላሜሕን ግን ሰባ ጊዜ ሰባት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ጕልማሳውን ለቁስሌ፤ ብላቴናውንም ለመወጋቴ ገድዬዋለሁና፤ ቃየንን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፤ ላሜሕን ግን ሰባ ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል። |
እግዚአብሔርም ለእርሱ፥ “እንዲህስ አይሆንም! ማንም ቃየንን የሚገድል፥ ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ጌታም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት።