ዘፍጥረት 4:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላሜሕም ለሚስቶቹ፥ “ዓዳ እና ጺላ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ሆይ፥ የምለውን ስሙኝ፤ ቢያቆስለኝ ጐልማሳውን ገደልኩ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገደልኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላሜሕ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “ዓዳና ሴላ ሆይ ስሙኝ፤ የላሜሕ ሚስቶች ሆይ አድምጡኝ፤ አንድ ሰው ቢያቈስለኝ፣ ጕልማሳው ቢጐዳኝ፣ ገደልሁት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላሜክ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤ እናንተ “ዓዳ እና ጺላ የላሜክ ሚስቶች ሆይ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ የምለውን ስሙ፤ አንድ ወጣት መትቶ ስላቈሰለኝ ገደልኩት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፥ “እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬንም አድምጡ፤ እኔ ጐልማሳውን ስለ መቍሰሌ፤ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገድየዋለሁና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፤ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬን አድምጡ፤ |
ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፥ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምጽን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ የሴኬም ነዋሪዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ፤