ዘፍጥረት 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጺላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እኅት ናዕማ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጺላም “ቱባልቃይን” የተባለ ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሱ ከነሐስና ከብረት ልዩ ልዩ ዐይነት ዕቃዎችን ይሠራ ነበር። ቱባልቃይንም ናዕማ የተባለች እኅት ነበረችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴላም ደግሞ ቶቤልን ወለደች። እርሱም ናስና ብረትን የሚሠራ ሆነ። የእኅቱም ስም ኖሄም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች፤ የቱባልቃይንም እኅት ናዕማ ነበረች። |
ላሜሕም ለሚስቶቹ፥ “ዓዳ እና ጺላ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ሆይ፥ የምለውን ስሙኝ፤ ቢያቆስለኝ ጐልማሳውን ገደልኩ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገደልኩ፤
አሁንም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልሃተኞች ጋር አብሮ የሚሆን፥ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ሐምራዊውንና ቀዩን ሰማያዊውንም ግምጃ የሚሠራ፥ ቅርጽንም የሚያውቅ ብልሃተኛ ሰው ላክልኝ።
ሳይጎድልህ እንጀራን ወደምትበላባት፥ አንዳችም ወደማታጣባት ምድር፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር ያስገባሃል።