ዘፍጥረት 39:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል ዐብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የጌታው ሚስት ልብሱን ይዛ “ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሱን ይዛ፥ “ና ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ። |
እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፥ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።