ዘፍጥረት 30:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልያ ባርያ ዘለፋም ወንድ ልጅን ለያዕቆብ ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልያ አገልጋይ ዘለፋም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልያ አገልጋይ ዚልፋ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልያ አገልጋይ ዘለፋም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የልያ ባሪያ ዘለፋም ወንድ ልጅን ለያዕቆብ ወለደች። |
“የጋድ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥
የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥