ጌታ እግዚአብሔርም ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ አንዳች እንዳትበሉ አዝዞአልን?” አላት።
ዘፍጥረት 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም እባቡን አለው፦ “ይህን በማድረግህ፥ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ እባብን እንዲህ አለው፤ “ይህን ስለ ሠራህ፣ “ከከብቶችና ከዱር እንስሳት ሁሉ ተለይተህ የተረገምህ ሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ በደረትህ እየተሳብህ ትሄዳለህ፤ ዐፈርም ትበላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ እባቡን እንዲህ አለው፦ “ይህን በማድረግህ ከእንስሶችና ከአራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምክ ሁን፤ ከዛሬ ጀምሮ በደረትህ እየተሳብክ ሂድ፤ ዕድሜህን ሙሉ ዐፈር ብላ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፥ “ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ሁሉ፥ ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ሁን ፤ በደረትህና በሆድህም ትሄዳለህ፤ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረገህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህም ትሄዳለህ፤ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ። |
ጌታ እግዚአብሔርም ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ አንዳች እንዳትበሉ አዝዞአልን?” አላት።
ትዋረጃለሽ፥ መሬት ላይ ተደፍተሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም በዝግታ ከአፈር ይወጣል፤ ድምጽሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ድምፅ ይሆናል፥ ንግግርሽም ከአፈር በሹክሹክታ ይወጣል።
ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ጉዳት አያደርሱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል ጌታ።
ስለዚህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ርኩስ ከሆነው ትለያላችሁ፤ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ላይ በሚርመሰመሱ ነፍሳት ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ።
እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፥ በምድር እንደሚሳቡ ፍጥረታት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጋቸው ይመጣሉ፤ በፍርሃት ወደ ጌታ አምላካችን ይመጣሉ፥ ከአንተ የተነሣ ይፈራሉ።