ኢሳይያስ 65:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ጉዳት አያደርሱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል ጌታ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጕዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤” ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ተኲላና ጠቦት አብረው ይመገባሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብ ምግብ ትቢያ ይሆናል፤ እነርሱም በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም” ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ያንጊዜ ተኵላና በግ በአንድነት ይሰማራሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም፥” ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ተኵላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፥ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከት |