ዘፍጥረት 26:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ማዕድ አቀረበላቸው፥ በሉም ጠጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም ድግስ ደግሶ አበላቸው፤ አጠጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ፥ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ጠጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ማዕድ አቀረበላቸው፤ በሉም፤ ጠጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ማዕድ አቀረበላቸው በሉም ጠጡም። |
ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፥ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጠራ፥ እነርሱም ምግብ ተመገቡ፥ በዚያም በተራራ ሌሊቱን ሙሉ አሳለፉ።
የሙሴ አማት ይትሮም የሚቃጠል ቊርባንና መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሊመገቡ ከሙሴ አማት ጋር መጡ።