ዘፍጥረት 31:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)54 ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፥ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጠራ፥ እነርሱም ምግብ ተመገቡ፥ በዚያም በተራራ ሌሊቱን ሙሉ አሳለፉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም54 ያዕቆብ በኰረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው ዐደሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም54 በተራራውም ላይ ያዕቆብ መሥዋዕት አቀረበ፤ ሰዎቹን ሁሉ ጠርቶም ምግብ እንዲመገቡ አደረገ፤ ከበሉም በኋላ ሌሊቱን በዚያ አሳለፉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)54 ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን ሠዋ፤ ወንድሞቹንም ጠራ፤ እነርሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚያም በተራራው አደሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)54 ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን ሠዋ ወንድሞቹንም እንጀራ እንዲበሉ ጠራ እነርሱም እንጀራን በሉ በዚያም በተራራ አደሩ። ምዕራፉን ተመልከት |