ዘፍጥረት 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራውን በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ይሠራ ከነበረው ሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በስድስተኛው ቀን ፈጸመ፤ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኚው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። |
በእኔና በእስራኤል ልጆች መካከል የዘለዓለም ምልክት ነው፤ ጌታ ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ፈጥሮአልና፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው አርፎአልና፥ ተነቃቅቶአልና።’”
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ፥ እግርህን ወደ ሰንበት፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ጌታንም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ በራስህ መንገድህን ከመጓዝ፥ ፈቅድህንም ከመፈጸም፥ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላካችሁ ሰንበት ነው፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም አገልጋይህም፥ አገልጋይትህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ ወይም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ፥ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፥ አንተ እንደምታርፍ ሁሉ አገልጋይህና አገልጋይትህ እንዲያርፉ።