ዘፀአት 31:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በእኔና በእስራኤል ልጆች መካከል የዘለዓለም ምልክት ነው፤ ጌታ ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ፈጥሮአልና፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው አርፎአልና፥ ተነቃቅቶአልና።’” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ለዘላለም ምልክት ይሆናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ሠርቶ፣ በሰባተኛው ቀን ከሥራ ታቅቦ ዐርፏልና።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እኔ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ ከፈጠርኩ በኋላ ሰባተኛው ቀን ሥራዬን አቁሜ ያረፍኩበት ስለ ሆነ በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር ምልክት ይሁን።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ሥራውን ፈጽሞ ስላረፈ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘለዓለም ምልክት ነው።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ስላረፈና ስለ ተነፈሰ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ምልክት ነው። ምዕራፉን ተመልከት |