ዘፍጥረት 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያም ስፍራ አስቀድሞ መሠውያ የሠራበት ነው፥ በዚያም አብራም የጌታን ስም ጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመጀመሪያ ጊዜም መሠዊያ ካቆመበት ስፍራ ደረሰ፤ በዚያም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሠዊያም ሠርቶበት የነበረው ነው፤ እዚያም አብርሃም እግዚአብሔርን አመለከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስፍራውም አስቀድሞ መሠውያ የሠራበት ነው፤ በዚያም አብራም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ስፍራ አስቀድሞ መሠውይ የሠራበት ነው በዚያም አብራም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። |
የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥
በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር፤