ዘፍጥረት 1:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር የምድር አራዊትን በየዐይነቱ፥ እንስሶችን በየዐይነታቸው በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችን በየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የምድር አራዊትን እንደየወገኑ፥ እንስሳትንም እንደየወገኑ፥ በምድር የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ እንደየወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። |
ምድሪቱን በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ለዓይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።