ገላትያ 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ መልካም ለሆነ ነገር ሁሉ ብትቀኑ መልካም ነው፤ ነገር ግን እኔ ከእናንተ ጋር ባለሁበት ጊዜ ብቻ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለበጎ እስከ ሆነ ድረስ ተቈርቋሪ መሆን መልካም ነው፤ ይህም መሆን የሚገባው ዘወትር እንጂ እኔ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ብቻ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓላማው ጥሩ ከሆነ መትጋት ምንጊዜም መልካም ነው፤ ነገር ግን ይህ መትጋታችሁ እኔ ከእናንተ ጋር በምኖርበት ጊዜ ብቻ አይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቅናትስ ዘወትር ለመልካም ሥራ ልትቀኑ ይገባል፤ ነገር ግን እኔ ከእናንተ ዘንድ ባለሁበት ጊዜ ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ በምኖርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በመልካም ነገር ተፈላጊ ብትሆኑ መልካም ነው። |
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ብቻ ኑሩ፤ በዚህም መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል እምነት አብራችሁ መጋደላችሁንና በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን እሰማለሁ።
ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።