እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፤ “ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፤ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፤
ዘዳግም 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላካችን በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን ገብቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካችን በሲና ተራራ ላይ ቃል ኪዳን አደረገ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁ እግዚአብሔር በኮሬብ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኑን አጸና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። |
እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፤ “ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፤ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፤
እርሱም እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉና በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገ ተአምራት ፊት አደርጋለሁ፤ እኔ በአንተ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝብ ሁሉ የጌታን ሥራ ያያል።
ይህንንም ከግብጽ አገር ከብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝኩት ቃላት ነው፤ አልሁም፦ ድምፄን ስሙ፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።
እጃቸውን ይዤ ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ አደረግሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እኔ ገዢአቸው ብሆንም እንኳ ያን ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፥ ይላል ጌታ።
“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ፦
ጌታ አምላካችሁ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ ጌታ አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም መልክ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።