ዘዳግም 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራራው በጥቍር ደመናና በድቅድቅ ጨለማ ተውጦ ሳለ ነበልባሉ ሰማይ እስከሚደርስ ድረስ በተቃጠለ ጊዜ መጥታችሁ ከተራራው ግርጌ ቆማችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስከ ሰማይ በሚደርስ የእሳት ነበልባልና ጥቅጥቅ ባለ የጢስ ደመና ወደተጋረደው ተራራ ግርጌ ቀርባችሁ ቆማችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፤ ተራራውም እስከ ሰማይ ድረስ በእሳት ይነድድ ነበር፤ ጨለማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅድቅ ጨለማም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፤ እስከ ሰማይም መካከል ድረስ አሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማም ነበረ። |
ጌታም ሙሴን፦ “ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙና ለዘለዓለም እንዲያምኑህ፥ እነሆ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለጌታ ነገረ።
“ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ሁሉ፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ፥