ዘዳግም 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደ የማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን አንገት ይስበሩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን ዐንገት ይስበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋንም ጨርሶ ወዳልታረሰና ምንም ተክል ወዳልተተከለበት፥ ወንዙም ወደማይደርቅበት ሸለቆ ይዘዋት ወርደው በዚያ አንገትዋን በመቈልመም ይስበሩት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያችም ከተማ ሽማግሌዎች ጊደሪቱን ይዘው ፈሳሽ ውኃ ወዳለበት ወዳልታረሰና ዘርም ወዳልተዘራበት ሽለቆ ይሄዳሉ፤ በዚያም በሸለቆው ውስጥ የጊደሪቱን ቋንጃዋን ይቈርጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያችም ከተማ ሽማግሌዎች ጊደሪቱን ይዘው ፈሳሽ ውኃ ወዳለበት ወዳልታረሰና ዘርም ወዳልተዘራበት ሸለቆ ይሄዳሉ፤ በዚያም በሸለቆው ውስጥ የጊደሪቱን አንገት ይሰብራሉ። |
እንዲያገለግሉና በጌታ ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ አምላክህ ጌታ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።
ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው።