ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፥ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ያእዜር ሄዱ፤
ዘዳግም 2:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአርኖን ሸለቆ ጫፍ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆው ውስጥ ከምትገኘዋ ከተማ አንሥቶ እስከ ገለዓድ ካሉት ከተሞች አንዳቸውም እንኳ ሊገቱን አልቻሉም። አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአርኖን ቈላ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ ማናቸይቱም ከተማ አልጠነከረችብንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ ሰጠን። |
ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፥ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ያእዜር ሄዱ፤
እርሱም የያዘው ግዛት፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ አሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ፥ የሮቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል።
ድንበርህንም ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረበዳ እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፥ ከፊትህ ታባርራቸዋለህ።
በዚያን ወቅት ይህችን ምድር በወረስን ጊዜ፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠኋቸው።
በሐሴቦን የተቀመጠው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፥ ይገዛ የነበረው በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ሲሆን፥
ጌታም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ማንም ሰው ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ ጌታም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረበት በዚያን ጊዜ ስለምን አልወሰዳችኋቸውም?