Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 17:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከተሞችዋ ለዘለዓለም ባድማ ይሆናሉ፤ ለመንጋ ማሰማርያ ይሆናሉ፤ መንጎች በዚያ ያርፋሉ የሚያስፈራቸውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የሶርያ ከተሞች ሰው የማይኖርባቸው ባድማዎች ይሆናሉ፤ በጎችና ከብቶች በዚያ ይሰማራሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ለመ​ንጋ ማሰ​ማ​ር​ያም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከተሞችዋ ለዘላለም የተፈቱ ይሆናሉ፥ ለመንጋ ማሰማርያ ይሆናሉ፥ መንጎች በዚያ ያርፋሉ የሚያስፈራቸውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 17:2
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ራባን የግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድርም አራዊት መብል ይሆናል፥ የሚያስፈራራቸውም የለም።


የባሕሩም ዳር የግጦሽ መሬት፥ የእረኞች መስክና የበጎች በረት ይሆናል።


እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም፤ የሠራዊት ጌታ አፍ ተናግሮአልና።


በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።


የጋድም ልጆች ዲቦንን፥ አጣሮትን፥ አሮዔርን ሠሩ፤


በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል?፥ ብለሽ ጠይቂ።


በዚያን ወቅት ይህችን ምድር በወረስን ጊዜ፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠኋቸው።


በዚያን ቀን፤ አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በግ ብቻ ይተርፈዋል።


በጎችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደሚሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤ የበግ ጠቦቶችም በባለጠጎች ፍርስራሽ ላይ ሣር ይበላሉ።


ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ የሜድባ ሜዳ ሁሉ፥


ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፥ ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል።


ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ።


የተመሸገችው ከተማ ብቻዋን ሆነች፤ እንደ ምድረ በዳ ሆና የተተወች መኖሪያ ሆናለች፤ በዚያም ጥጃ ይሰማራል፥ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።


ማንም ሳያስፈራቸው በምድራቸው በሰላም በተቀመጡ ጊዜ፥ እፍረታቸውንና የበደሉኝን በደላቸውን ይሸከማሉ።


ግዛታቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት ለፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች