ጌታ ይህን ምልክት ይሰጣል፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱ ላይ ያለውም ዐመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካይነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይህ እንደ ተፈጸመ ወዲያውኑ ትገነዘባለህ’” አለ።
ዘዳግም 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፥ ‘አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው’ ቢልህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፣ “አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው” ቢልህ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አደርጋለሁ ብሎ የተናገረውን ተአምርና ድንቅ ነገር ቢያደርግም እንኳ፥ አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል፤ እናምልካቸውም ቢልህ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ብሎ የተናገረህ ምልክቱ ወይም ተአምራቱ ቢፈጸም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ቢልህ፥ |
ጌታ ይህን ምልክት ይሰጣል፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱ ላይ ያለውም ዐመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካይነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይህ እንደ ተፈጸመ ወዲያውኑ ትገነዘባለህ’” አለ።
እነሆ፥ ሐሰትን ትንቢት በሚያልሙ በሚናገሩም፥ በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ፤ እኔም አልላክኋቸውም አላዘዝኋቸውምም፥ ለእነዚህም ሕዝብ በማናቸውም ነገር አይጠቅሙአቸውም፥ ይላል ጌታ።
እናንተ ግን፦ ለባቢሎን ንጉሥ አታገለግሉም የሚሉአችሁን ነብዮቻችሁንና ምዋርተኞቻችሁን፥ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ቃላተኞቻችሁን መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤
ተራፊም ትርጒም አልባ ነገር ተናግረዋል፥ ሟርተኞችም ሐሰተኛ ራእይ አይተዋል፤ የሚያሳስቱ ሕልሞችን ተናግረዋል፤ ባዶ ማጽናኛም ሰጥተዋል፤ ለዚህም ነው እረኛም ስለ ሌላቸው እንደ በጎች የተቅበዘበዙትና የተጨነቁት።
“የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥
ነቢዩ በጌታ ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገለጸ፥ መልእክቱ ጌታ የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።”